Category: News

ስምንት የወላድ እናቶች ማቆያ ማዕከላት ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኑ።

ማዕከላቱ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ KOFIH ፕሮጀክት እና በጅማ ዞን ጤና ቢሮ ጥምረትና ትብብር በዴዶ፣ ኦሞናዳ፣ ኦሞቤየም እና ማንቾ ወረዳ በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች የተገነቡ ናቸው። የወላድ እናቶች ማቆያ ማዕከላቱን ለመገንባት 13 ነጥብ 6 ሚሊዮን እንዲሁም አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ከ700 ሺህ ብር በላይ በጥቅሉ ከ 14 ሚሊዮን 300 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጎዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል […]

የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም በጤናው ዘርፍ ለውጥ እያመጣ ነው።

የዋና ዋና ከተሞች የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈፃፀም ሀገራዊ የግምገማ መድረክ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል። ፕሮግራሙ በሀገሪቱ ስድስት ዋና ዋና ከተሞች ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ ሀረማያ፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ እና መቀሌ እየተተገበረ ያለ ነው። በግምገማ መድረኩ የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እስካሁን ያለው አፈፃፀም መልካም መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙ ዜጎች ሆስፒታል […]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ KOFIH ፕሮጀክት 48 የጤና ባለሙያዎችን አሰልጥኖ አስመረቀ፡፡

ሰልጣኞቹ በዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት አዳራሽ ተገኝተዉ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ዴቨሎፕመንት ም/ፕሬዝደንት አቶ ኮራ ጡሽኔ ኮሪያ ፋዉንዴሽን ፎር ኢንተርናሽናል ሄልዝ (KOFIH) ላለፉት አምስት አመታት በጅማ ዞን የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናዉን መቆየቱን ገልፀዋል፡፡ የጤና አገልግሎት ግቦችን ለማሳካት በፕሮጀክቱ የተሰጠዉ ስልጠና ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ያገኘዉን እዉቀት ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ስርዓት ለማሻሻል […]

ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎች

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚገባቸዉ ተነገረ፡፡ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን ጅማ ዩኒቨርሲቲ አስታዉቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ የ ECDD ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲሴቢሊቲ ዴቨሎፕመንት ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተክሌ፣ የ ECDD ቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሴኔት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸዉ […]

5ሺህ የፒ. ኤች. ዲ ምሩቃን፣ በ5ዓመት

በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች 5ሺህ ፒ.ኤች.ዲ ምሩቃንን ለማፍራት እየተሰራ ነዉ፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፒ.ኤች.ዲ እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ባላቸዉ ምሁራን መካከል ዉይይት ተካሂዷል፡፡ በምርምር እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት የተመረጡ አስር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበርካታ ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ተለይተዉ ተዘጋጅተዋል፡፡ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማእድን፣ የኢንፎረሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና የቱሪዝም ዘርፎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የተሰጣቸዉ […]

የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ግንዛቤ

ተማሪዎች ከግቢ ዉጪ እንዳይንቀሳቀሱ ተጥሎ የነበረዉ ገደብ ተነሳ፡፡ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮሎች ግንዛቤ መፍጠሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አራቱም ካምፓሶች ተካሂዷል። ዝግጅቱ በጅማ አደጋ ግዜ ክወና ማዕከል አዘጋጅነት “ሁልግዜ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በመጠቀም የኮቪድ-19 መተላለፊያ ሠንሰለትን እበጥሳለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ ተከናዉኗል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ በዝግጅቱ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለፁት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው […]

17ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ

ሙስናን ለመከላከል በምርምርና ሳይንሳዊ ትንተና መታገዝ ተገቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡ 17ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የትውልድ የስነምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዞአችንን እናፋጥናለን በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል፡፡ የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሴኔት አባላት እና […]

የጅማ ዩኒቨርሲተ ከፍተኛ አመራሮች የቴክኖሎጂ መንደር ጉብኝት

በሀገራችን ኢትዮጵያ የስንዴ ፍጆታን በሀገር ዉስጥ ምርት ለመሸፈንና ከዉጭ የሚገባዉን ለማስቀረት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲተ ከፍተኛ አመራሮች በዴዶ ወረዳ ኢላላ ቀበሌ በሚገኙ አርሶ አደሮች በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በጅማ ዞን አምስት ወረዳዎችን በመምረጥ የቴክኖሎጂ መንደር በማቋቋም ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ሳነቴ የተባለ የዋግ […]

የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደቀጠለ ነዉ፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ለሻሎም ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡ ብዛታቸዉ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ የሆኑ የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና አልባሳት በድጋፍ መልክ ተሰጥተዋል፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር መሀመድ መጫ የተደረገዉ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘላቂ ባለመሆኑ ወደፊት በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ ድጋፉን የተቀበለዉ ሻሎም […]

የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራኑ ተሰጠ

የመማር ማስተማር ሂደት ማስቀጠያ አካል የሆነዉ የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራን ተሰጠ፡፡ ገለፃዉ የሳይኮሶሻል ድጋፍና ስነ-ልቦና ጤና በኮቪድ-19 ወቅት በሚል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ባዘጋጁት መመሪያ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡ በጅማ በሁሉም ኮሌጆች ላሉ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ገለፃና ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የመርሃ ግብሩ መዘጋጀት ተማሪዎች ዉጤታማ ሆነዉ ትምህርታቸዉን እንዲያጠናቅቁ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል […]