5ሺህ የፒ. ኤች. ዲ ምሩቃን፣ በ5ዓመት

በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች 5ሺህ ፒ.ኤች.ዲ ምሩቃንን ለማፍራት እየተሰራ ነዉ፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፒ.ኤች.ዲ እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ባላቸዉ ምሁራን መካከል ዉይይት ተካሂዷል፡፡
በምርምር እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት የተመረጡ አስር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበርካታ ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ተለይተዉ ተዘጋጅተዋል፡፡
የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማእድን፣ የኢንፎረሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና የቱሪዝም ዘርፎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የተሰጣቸዉ የትኩረት አቅጣቻዎች ናቸዉ፡፡
እ.አ.አ ከ2021 እስከ 2025 ባሉት አምስት አመታት 5ሺህ በፒ.ኤች.ዲ. ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በመጀመሪያዎቹ ሁለት አመታት ሰልጣኞችን ተቀብለዉ ማሰልጠን እንደሚጀምሩ ተገልፅዋል፡፡
የአግሮኖሚ፣ ሂዉማን ኒዉትሪሽን፣ ሴራሚክ ኢንጂነሪንግ፣ ኢንዱስትሪያል ኢኮኖሚክስ እና ኢኮ-ቱሪዝም ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሆስትነት የተመረጠባቸዉ ዋነኛ ዘርፎች እንደሆኑ በዉይይት መድረኩ ተነስቷል፡፡
በመድረኩ በርካታ ሃሳቦች ተነስተዉ ዉይይት የተደረገባቸዉ ሲሆን መድረኩ የተለያዩ ግብረ-መልሶች የተሰበሰቡበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
የውይይት መድረኩን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ የመሩት ሲሆን የዩኒቨርስቲው የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክተሩ ፕሮፌሰር ተፈራ በላቸው የውይይት መነሻ ሀሳብ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል ።