COVID-19 Updates

COVID-19 Updates


ኮሮናቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) በSARS-CoV-2 ቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ተላላፊ በሽታ ነው።አብዛኞቹ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች የሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ የሚደርሱ ሲሆኑ ምንም ህክምና ሳይደረግላቸው ሊድኑ ይችላሉ። ነገር ግን፣ የተወሰኑ ሰዎች በጠና ሊታመሙ እና ህክምና ሊያስፈልጋቸው ይችላል።


እንዴት እንደሚተላለፍቫይረሱ ታማሚ ሰው ሲያስል፣ ሲያስነጥስ፣ ሲናገር፣ ሲዘምር ወይም ሲተነፍስ ከአፍ ወይም ከአፍንጫ በሚወጡ አነስተኛ ፈሳሽ ቅንጣቶች መልክ ሊሰራጭ ይችላል። እነዚህ ቅንጣቶች ከትልልቅ የመተንፈሻ አካላት ነጠብጣቦች እስከ አነስተኛ የአየር ላይ ብናኞች ያካትታል።ኮቪድ-19 ከያዘው ሰው በቅርብ ርቀት ከተገኙ ሰዎች በትንፋሽ አማካኝነት፣ ወይም በቫይረሱ የተበከለ ነገር ከነኩ በኋላ አይንዎን፣ አፍንጫዎን ወይም አፍዎን በመንካት በሽታው ሊተላልፍብዎት ይችላል። ቫይረሱ በቤት ውስጥ ወይም በተፋፈጉ ሁኔታዎች በቀላሉ ይሰራጫል።