Category: News

የጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ስልጠና

በኦሮሞ ፍክሎርና ስነ-ፅሁፍ እና ታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍሎች ለጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች በባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ማሰባሰብና ማስተዳደር ዘዴ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡ በስልጠናዉ መጀመሪያ ላይ የጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ አወል እንዳሉት ጅማ ዩኒቨርሲቲ የቢሯችንን እንቅስቃሴ መደገፍ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነዉ ብለዋል፡፡ በባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ምንነት፣ አሰባሰብ እና […]

ለሴት አካዳሚክ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡

Network for Advancement of Sustainable Capacity in Education and Research in Ethiopia (NASCERE) ፕሮግራም ለ15 ቀናት በሚሰጠዉ የአቅም ማጎልበት ስለጠና ላይ ከ35 በላይ ሴት መምህራን በመሳተፍ ላይ ናቸዉ፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ ጥቂት ፒ.ኤች.ዲ የያዙ ሴት መምህራን ባሉበት; አገራዊ ሁኔታ የስልጠናው ተሳታፊዎች ይህንን እድል በመጠቀም ለዉጥ የሚያመጣ ገዢ ሃሳብ አፍልቀዉ ራሳቸዉን ለስኬት […]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ለሃገር ጥሪ ምላሽ የመስጠት አካል የሆነው ድጋፍ ዛሬም ተደርጉዋል። ዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ ዋጋቸው ከ 600 ሺህ ብር በላይ የሆነ 80 ኩንታል ምስር እና 80 ኩንታል የቅንጬ እህል ድጋፍ አድርጉዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ይህ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንደሆነ ገልፀው መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚወስደው እርምጃ ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር፣ የመማር ማስተማር እና […]

ደማችን ለሃገሩ ክብር ለደማው መከላከያ ሰራዊታችን

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለቀረበው ሃገራዊ ጥሪ ምላሽ የደም ልገሳ አድርገዋል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው እለት ከሠራተኞች ጋር ባደረገው ውይይት 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችም በበከåላtው በእውቀት፣ በገንዘብና በደም ልገሳ እንዲሁም ሙያዊ አገልግሎት ለማበርከት ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የዚሁ አበርክቶት አካል የሆነውን የደም ልገሳ ስነ-ስርዓት […]

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱ ላይ ከ 3ሺህ በላይ የሚሆኑ የሴኔት፣ የአካዳሚክ፣ አስተዳደር ሰራተኞችና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡ መድረኩ የተዘጋጀው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ መንግስት የሀገር ሉዓላዊነትንና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ እየሰራ ስለሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለሀገር ሊያበረክት የሚችለዉን አስተዋፅዖ አስመልክቶ ሃሳቦችን ለመለዋወጥና ሙያዊና ቁሳዊ ድጋፎችን ለማሰባሰብ እንደሆነ ተገልፅዋል፡፡ ይኸዉም ቀጥታ የገንዘብና ቁሳዊ ድጋፎችን፣ የህክምና […]

የግቢ ጽዳትና ውበት ንቅናቄ በጅማ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪዎችን የመቀበል ሂደት አካል የሆነው የግቢ ጽዳትና ውበት ንቅናቄ ተካሂዷል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው አመት ሁለንተናዊ የግቢ ጽዳትና ውበት ለውጥ ለማምጣት አቅጣጫ አስቀምጦ የንቅናቄ መርሃ-ግብር አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ታውቋል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጽዳትና ውበት ስራን በዛሬው እለት ሲያከናውን ውሏል። የተማሪዎች መኝታ፣ መመገቢያ፣ መማሪያ እና መዝናኛ […]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለወገን የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ዛሬም በጅማ ከተማ የተባበሩት አካባቢ በቀድሞ አጠራሩ ኢዲዲሲ ዉስጥ ለሚኖሩ ከ 450 በላይ አባወራዎች ፍራሾች፣ ምግብና ምግብ ነክ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሁኔታ እና አጋጣሚዎች ለህብረተሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በዛሬዉ እለትም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክስ እና አስተዳደር ሰራተኞች ድጋፍ ግምታቸዉ ከ 500 ሺህ ብር በላይ የሆኑ ፍራሽ፣ የምግብ እህልና […]

ተማሪዎችን ለመቀበል የኮቪድ-19 የጥንቃቄ ዉይይት

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት ስር የሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ፡፡ ዉይይቱ የ2013ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላን አስመልክቶ ሊደረጉ ስለሚገባቸዉ ጥንቃቄዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ታዉቋል፡፡ የጥበቃና ደህንነት፣ የጠቅላላ አገልግሎት፣ የተማሪዎች መኝታ ተቆጣጣሪዎች፣ የተማሪዎች ካፍቴሪያ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች፤ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሲመጡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከግምት ዉስጥ ያስገባ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን […]

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለሀገር እድገት

የሃገር ሁለንተናዊ እድገትን ለማፋጠን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀምና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተነገረ፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በትብብር መስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ተፈራርመዋል፡፡ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የዩኒቨርሲቲዉን አብይ የትኩረት አቅጣጫ የሆኑት መማር […]

እጅ ለእጅ ስንያያዝ ይበልጥ እንደምቃለን! ዶ/ር ጀማል አባፊጣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት

የኮቪድ – 19 ምላሽ የፈጠራ ስራዎች ዓውደ-ርዕይ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጉባኤ አስተባባሪዎች የእውቅና እና ምስጋና ፕሮግራም በሃጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ ማዕከል ተካሂዷል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በየደረጃው የሚገኙ ሰራተኞቹ ጥረትና ያልተቆጠበ አስተዋፅዎ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ አንድ ተቋም ያለሰራተኞቹ ትጋትና […]