የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራኑ ተሰጠ

የመማር ማስተማር ሂደት ማስቀጠያ አካል የሆነዉ የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራን ተሰጠ፡፡
ገለፃዉ የሳይኮሶሻል ድጋፍና ስነ-ልቦና ጤና በኮቪድ-19 ወቅት በሚል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ባዘጋጁት መመሪያ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡
በጅማ በሁሉም ኮሌጆች ላሉ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ገለፃና ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የመርሃ ግብሩ መዘጋጀት ተማሪዎች ዉጤታማ ሆነዉ ትምህርታቸዉን እንዲያጠናቅቁ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡
በኪቪድ-19 ወረርሽኝ ምክኒያት ትምህርት ከተቋረጠ በኋላ ተማሪዎች ከትምህርት ርቀዉያ ለፉት 9 ወራት በተለያዩ ሁኔታዎች ዉስጥ እያሳለፉ መሆናቸዉ ተነስቷል፡፡
ከተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎች ወጥተዉ ወደ ትምህርት ገበታ ሲመለሱ ሊያጋጥሟቸዉ የሚችሉትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍና ዉጤታማ ሆነዉ ትምህርታቸዉን እንዲያጠናቅቁ ለማድረግ የመምህራኑ ዝግጁነት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በኪቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ትምህርት መማር በራሱ የሚፈጥረዉ ስነ-ልቦናዊ ጫና የምኖረዉ መሆኑና የትምህርት አሰጣጥ ስርዓቱ የባከነዉን ግዜ ለማካካስ አጭር ግዜ ከመሆኑጋር በተገናኘ ተማሪዎች የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጫናዎች ቢገጥሟቸዉ መፍትሄ ለመሻትና አስፈላጊዉን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ገለፃ እና ስልጠናዉ መምህራኖቹ ዝግጁ እንዲሆኑ ያስችላል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡