Author: erouser

5ሺህ የፒ. ኤች. ዲ ምሩቃን፣ በ5ዓመት

በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች 5ሺህ ፒ.ኤች.ዲ ምሩቃንን ለማፍራት እየተሰራ ነዉ፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፒ.ኤች.ዲ እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ባላቸዉ ምሁራን መካከል ዉይይት ተካሂዷል፡፡ በምርምር እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት የተመረጡ አስር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበርካታ ዘርፎች ስልጠና ለመስጠት ተለይተዉ ተዘጋጅተዋል፡፡ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማእድን፣ የኢንፎረሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና የቱሪዝም ዘርፎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የተሰጣቸዉ […]

የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ግንዛቤ

ተማሪዎች ከግቢ ዉጪ እንዳይንቀሳቀሱ ተጥሎ የነበረዉ ገደብ ተነሳ፡፡ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮሎች ግንዛቤ መፍጠሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አራቱም ካምፓሶች ተካሂዷል። ዝግጅቱ በጅማ አደጋ ግዜ ክወና ማዕከል አዘጋጅነት “ሁልግዜ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በመጠቀም የኮቪድ-19 መተላለፊያ ሠንሰለትን እበጥሳለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ ተከናዉኗል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ በዝግጅቱ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለፁት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው […]

17ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ

ሙስናን ለመከላከል በምርምርና ሳይንሳዊ ትንተና መታገዝ ተገቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡ 17ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የትውልድ የስነምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፒሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዞአችንን እናፋጥናለን በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል፡፡ የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሴኔት አባላት እና […]

የጅማ ዩኒቨርሲተ ከፍተኛ አመራሮች የቴክኖሎጂ መንደር ጉብኝት

በሀገራችን ኢትዮጵያ የስንዴ ፍጆታን በሀገር ዉስጥ ምርት ለመሸፈንና ከዉጭ የሚገባዉን ለማስቀረት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲተ ከፍተኛ አመራሮች በዴዶ ወረዳ ኢላላ ቀበሌ በሚገኙ አርሶ አደሮች በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በጅማ ዞን አምስት ወረዳዎችን በመምረጥ የቴክኖሎጂ መንደር በማቋቋም ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ሳነቴ የተባለ የዋግ […]

የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደቀጠለ ነዉ፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ለሻሎም ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡ ብዛታቸዉ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ የሆኑ የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና አልባሳት በድጋፍ መልክ ተሰጥተዋል፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር መሀመድ መጫ የተደረገዉ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘላቂ ባለመሆኑ ወደፊት በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ ድጋፉን የተቀበለዉ ሻሎም […]

የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራኑ ተሰጠ

የመማር ማስተማር ሂደት ማስቀጠያ አካል የሆነዉ የሳይኮሶሻል ገለፃና ስልጠና ለመምህራን ተሰጠ፡፡ ገለፃዉ የሳይኮሶሻል ድጋፍና ስነ-ልቦና ጤና በኮቪድ-19 ወቅት በሚል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ባዘጋጁት መመሪያ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡ በጅማ በሁሉም ኮሌጆች ላሉ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ገለፃና ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የመርሃ ግብሩ መዘጋጀት ተማሪዎች ዉጤታማ ሆነዉ ትምህርታቸዉን እንዲያጠናቅቁ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል […]

የጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ስልጠና

በኦሮሞ ፍክሎርና ስነ-ፅሁፍ እና ታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍሎች ለጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች በባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ማሰባሰብና ማስተዳደር ዘዴ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡ በስልጠናዉ መጀመሪያ ላይ የጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ አወል እንዳሉት ጅማ ዩኒቨርሲቲ የቢሯችንን እንቅስቃሴ መደገፍ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነዉ ብለዋል፡፡ በባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ምንነት፣ አሰባሰብ እና […]

ለሴት አካዳሚክ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡

Network for Advancement of Sustainable Capacity in Education and Research in Ethiopia (NASCERE) ፕሮግራም ለ15 ቀናት በሚሰጠዉ የአቅም ማጎልበት ስለጠና ላይ ከ35 በላይ ሴት መምህራን በመሳተፍ ላይ ናቸዉ፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ ጥቂት ፒ.ኤች.ዲ የያዙ ሴት መምህራን ባሉበት; አገራዊ ሁኔታ የስልጠናው ተሳታፊዎች ይህንን እድል በመጠቀም ለዉጥ የሚያመጣ ገዢ ሃሳብ አፍልቀዉ ራሳቸዉን ለስኬት […]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ለሃገር ጥሪ ምላሽ የመስጠት አካል የሆነው ድጋፍ ዛሬም ተደርጉዋል። ዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ ዋጋቸው ከ 600 ሺህ ብር በላይ የሆነ 80 ኩንታል ምስር እና 80 ኩንታል የቅንጬ እህል ድጋፍ አድርጉዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ይህ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንደሆነ ገልፀው መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚወስደው እርምጃ ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር፣ የመማር ማስተማር እና […]

ደማችን ለሃገሩ ክብር ለደማው መከላከያ ሰራዊታችን

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለቀረበው ሃገራዊ ጥሪ ምላሽ የደም ልገሳ አድርገዋል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው እለት ከሠራተኞች ጋር ባደረገው ውይይት 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችም በበከåላtው በእውቀት፣ በገንዘብና በደም ልገሳ እንዲሁም ሙያዊ አገልግሎት ለማበርከት ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የዚሁ አበርክቶት አካል የሆነውን የደም ልገሳ ስነ-ስርዓት […]