HDP ለጤናዉ ዘርፍ ባለሙያዎች

HDP ለጤናዉ ዘርፍ ባለሙያዎች
ሚያዝያ 10/2013 ዓ.ም
**************************
የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ከጤና ባለሙያች የስራ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ መሆን ይገባዋል ተባለ፡፡
የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP) ከገፅ ለገፅ ትምህርት በተጨማሪ በበየነ-መረብ (ኦንላይን) ለመስጠት የሚያስችል ፓይለት ፕሮግራም ተጀመረ፡፡
የከፍተኛ ዲፕሎማ ፓይለት ፕሮግራም በዉጭ ገምጋሚዎች ታይቶ የተሰጠበት አስተያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ተፈራ ታደሰ ለዉይይት ቀርቧል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አዲስዓለም ታዬ ላለፉት አስር ወራት ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ሳይንስና ከፍተኛ ተርምህርት ሚኒስቴር እና ጃፒዬጎ (Jhpiego) የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራምን ለጤናዉ ዘርፍ ባለሙያዎች እንዲመች ለማድረግ ሲሰሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ፕሮግራም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፋፋት እየሰራ እንደሆነ የገለፁት አቶ አዲስዓለም በዉይይት መድረኩ የሚነሱ ሀሳቦችን በመቀመር ፕሮግራሙን ዉጤታማ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ አሳዉቀዋል፡፡
ፕሮግራሙ ከዚህ ቀደም በገፅ ለ ገፅ ትምህርት ሲተገበር በመቆየቱ የጤና ባለሙያዎች ከስራቸዉ ባህሪ አንፃር የገፅ ለ ገፅ ትምህርት ለመከታተል ሲቸገሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የማስተማሪያ ሞጁሎችን የማስተካከል እና በኢ-ለርኒንግ ፕላትፎርም ለአጠቃቀም በሚመች መልኩ ተሰድረዋል ተብሏል፡፡
በዉይይት መድረኩ የዘርፉ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት ተሳታፊ ነበሩ፡፡