የእጩ መልማይና ምርጫ ኮሚቴ

ኮሚቴው ዛሬ በ09/07/2011 ዓ. ም. ባካሄደው ስብሰባው የአመልካቾችን የትምህርት ደረጃ የመለየት፣ የስራ ልምዳቸውን የመለየትና ለስራ ልምዳቸው ደረጃ የመስጠት ስራ አከናውኗል፡፡ ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ከተቀበላቸው 10 (አስር) ተወዳዳሪዎች መካከል 9 (ዘጠኝ) ተወዳዳሪዎች ብቻ በውድድሩ እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

  1. ፕሮፌሰር ቂጤሳ ሁንዴራ
  2. ፕሮፌሰር አርጋው አምበሉ
  3. ዶ/ር አብዱ አባጊቤ
  4. ዶ/ር ጀማል አባፊጣ
  5. ዶ/ር ዘይኑ አህመድ
  6. ዶ/ር እውነቱ ሀይሉ
  7. ዶ/ር ሱልጣን ሱሌማን
  8. ዶ/ር ናቃቸው ባሹ እና
  9. ዶ/ር ገመዳ አበበ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡

 እንዲሁም ለአስተዳደርና የተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ የተቀበላቸው አራት አመልካቾች በውድድሩ እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡ እነዚህም፡-

  1. ዶ/ር ደሳለኝ በየነ
  2. ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ
  3. ዶ/ር ተክሉ ታፈሰ እና
  4. ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ ናቸው፡፡            

ኮሚቴው