ስነ-ምግባር 20ኛ ዓመት

ስነ-ምግባር 20ኛ ዓመት
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 12/2013 ዓ.ም
*******************************************
የፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮምሽን የተቋቀመበትን 20ኛ ዓመት መሠረት በማድረግ የጥያቄና መልስ ውድድር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ተካሄደ፡፡
ውድድሩ የስነምግባር ግንባታ በሁሉም አካላት ተገቢውን እይታ እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ያላቸው አካላት ሚናቸውን የሚያጠናክሩበት ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነዉ፡፡
በሀገራችን ከግዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የትውልድ የስነምግባር ውድቀት ተማሪዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡበት ለማድረግ በሁሉም የሀገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች መካከል የሥነ-ምግባር የጥያቄና መልስ ውድድር በማካሄድ ተማሪዎችን በማነቃቃት በሥነ-ምግባር ዙሪያ የሚኖራቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችን በመሸለም ተማሪዎቹ ለሌሎች እኩዮቻቸዉ አርዓያ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
የጅማ ዩኒቨርስቲ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት የመጀመሪያውን የካምፓስ የተማሪዎች የሥነምግባር የጥያቄና መልስ ውድድር ከህግና አስተዳደር እንዲሁም ከሶሻል ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ መምህራን በተሰየሙ ዳኞች አካሂዷል፡፡
የየካመፓሶቹ አሸናፊ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደዉ የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታዉቋል፡፡