News

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ህክምና ማዕከል ጉብኝት አደረጉ።

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የካንሠር ህክምና መስጫ ማዕከል፤ አዮ የተቀናጀ አምቡላንስ አገልግሎት፤ የኦክስጅን ማምረቻ፣ ማጣሪያና ማስተላለፊያ ፕላንት፤ የጅዩ-ሲምቦና ህክምና ቁሳቁስ ዲዛይን ላብራቶሪ እና በባዮሜዲካል ማዕከል የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች በጉብኝቱ ምልከታ ከተካሄደባቸው መካከል ናቸው። ሚኒስትር ድኤታው በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው አዮ የአንድ […]

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የትምህርት ዘመን ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ 1 ሺህ 409 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቨርቹዋል አስመረቀ፡፡

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የጅማ ከተማ ከንቲባና የዩኒቨርሲቲዉ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቲጃኒ ናስር እና የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የእለቱ ተመራቂዎችንና ቤተሰቦቻቸዉን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዉ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሀገራችን ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ መሆኑንና በተለይም በጤናዉ ዘርፍ […]

ከፍተኛ ትምህርትን መልሶ ስለማስጀመር

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ከፍተኛ ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመው የምልከታ ኮሚቴ ገለጸ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 11 ኮሚቴዎችን በማቋቋም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለመቀበል ምን ዝግጅት አድርገዋል በሚል ወቅታዊ አቋምን በመፈተሸ ላይ ይገኛል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት ተቋማቱ ከገፅ ለገፅ ትምህርት […]

ለሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በጅማ ከተማ ለሚገኘው ሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሰበሰበው ሃያ ዘጠኝ ሺ (29፣000) ብር የሚያወጡ የምግብ (5 ኩንታል ጤፍ፤ የጣሳ ዱቄት ወተቶችን) እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለአረጋዊያም መርጃ ማዕከሉ አስረክቧል፡፡ በስነስርዓቱም ላይ የየኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የተገኙ ሲሆን፤ […]

የአዮ የተቀናጀ የአምቡላንስ አገልግሎት ለድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ።

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 16፣2013 ዓ.ም) የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤን በማሻሻል የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ማዘመን የሚያስችል ፕሮግራም ይፋ ሆነ። የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል። አዮ አምቡላንስ (እናት አምቡላንስ) አገልግሎትም ስራውን በይፋ ጀምሯል። የአምቡላንስ አገልግሎቱ በጅማ ከተማ እና ዞን የሚገኙ ሁሉም አምቡላንሶች በአንድ ማዕከል ስር ሆነው አገልግሎት የሚሰጡበትን አሰራር […]

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና ቀረበላቸው

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 13፣ 2013ዓ.ም) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋና አቀረቡ። ፕሬዝደንቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ለሶስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠልና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ የተሠሩ የፈጠራ ስራዎች ዓውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ለዚህ ፕሮግራም ስኬታማነት የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ሃላፊነቶችን በመውሰድ ሲሰሩ ቆይተዋል። ዶ/ር ጀማል ስኬቱን ከአድካሚውና አስቸጋሪው […]

ለሶስት ቀናት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተካሔደው ዓዉደ-ርዕይ እና የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠልና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዓልሞ ሲመክር የነበረው መድረክ ተጠናቋል፡፡ የምክክር መድረኩ ገንቢ የሆኑ ግብዓቶች የተሰበሰቡበት፣ የከፍተኛ ትምህርትን ለማስቀጠል መሰረት የተጣለበትና በባለድርሻ አካላት የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነበር፡፡ ከዚሁ የውይይት መድረክ ጎን ለጎን በተካሔደውና 45 ዩኒቨርሲቲዎችና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በተሳተፉበት ዓዉደ-ርዕይ ላይ በቀረቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በቂ ልምድ የተወሰደባቸዉና በሀገር […]

Registration is open

ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛው መርሐግብር በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ የተለያዩ የስልጠና ዘርፎች አመልካቾችን ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመማር ፍላጐት ያላችሁና የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት ማሟላት የምትችሉ አመልካቾች ከመስከረም 13 – 26/2013ዓ.ም ድረስ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽ የተለቀቀውን የመመዝገቢያ ቅጽ ካላችሁበት ሆናችሁ በመሙላት አልያም በዩኒቨርስቲው ዋናው ሬጅስትራር ጽ/ቤት (ዋናው ካምፓስ) በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ […]

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አረንጓዴ አሻራ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የወንድማማችነት፣ የፍቅር እና የሠላም አደባባይ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች አረንጉዋዴ አሻራቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ችግኝ በመትከል አሳርፈዋል። የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ […]