የስነ-ምግባር ጥያቄ እና መልስ

የስነ-ምግባር ጥያቄ እና መልስ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 19/2013ዓ.ም
***************************************
በስነ-ምግባር የታነፁ ተማሪዎች ሙስናን በመፀየፍ የሀገር እድገት እውን እንዲሆን ከፍተኛ ተፅጥኖ አላቸዉ ተባለ፡፡
ለ2 ቀናት በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየዉ የስነ-ምግባር ጥያቄና መልስ ዉድድር ተጠናቋል፡፡
በዉድድሩ መጀመሪያ ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ እናኑ ጥላሁን ተማሪዎችን በስነ-ምግባር ማነፅ እና ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል የዉድድሩ ዓላማ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ከሁሉም ካምፓሶች የተዉጣጡ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም መሰረት በትምህርታቸዉ የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡና ፍላጎት ያላቸዉን ተማሪዎች በማስታወቂያ በመጥራት 61 የተመዘገቡ ስሆን ለማጣሪያ ዉድድር 8 ዎቹ ለመጀመሪያዉ ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡
ከነዚህም መካከል 4ቱ ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ተማሪዎች ለመጨረሻዉ ዙር ውድድር ማለፋቸዉ ተነግሯል፡፡
በዉድድር የቀረቡት ጥያቄዎች የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን በማስመልከት የተለያዩ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት በበርካታ ተቋማት ዉስጥ መሰል ፕሮግራሞችን ሲያካሂድ ነበር፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዉድድሩ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደዉ ዉድድር ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
በመጨረሻም ተወዳዳሪዎች፣ የዉድድሩ ዳኞች እና ለፕሮግራሙ መሳካት አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላት የምስክር ወረቀት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከወ/ሮ እናኑ ጥላሁን እጅ ተቀብለዋል፡፡