ምሁራን እና ተመራማሪዎች ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን በጎ ተፅዕኖ ልብ ሊሉ ይገባል፣ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ

ምሁራን እና ተመራማሪዎች ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን በጎ ተፅዕኖ ልብ ሊሉ ይገባል፣ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 16/2013ዓ.ም
*********************************
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 11ኛው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የምርምር ጉባዔ ተጠናቀቀ።
ጉባዔውን በንግግር የዘጉት የጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በሀገር በቀል እሴቶች ላይ የተመሠረተ እውቀት የግብርና ምርትን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ግጭቶችን ለመፍታት፣ ለህዝብ ጠቃሚ ፖሊሲዎችን ለማውጣትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሊተገበር የሚችል ነው ብለዋል።
ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ የሚያፈራቸው ምሁራን እና ተመራማሪዎች ማህበረሰቡ በእለት ከእለት ህይወቱ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች እና ሁነቶች ላይ ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን በጎ ተፅዕኖ ልብ ሊሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በጉባዔው የሁለተኛ ቀን ውሎ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በጉባዔው ላይ ፅሁፎችን ላቀረቡ እና በዩኒቨርሲቲያችን በተለያዩ ዘሪፎች ስያገለግሉ ለነበሩ ምሁራን፣ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እና የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ታደሠ ሀብታሙ እጅ የእዉቅና ሰርተፍኬት እና ስጦታዎችን ተቀብለዋል።
ሀገር በቀል እውቀቶች ብዝሃነት፣ ለእኩልነት እና ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የነበረው ጉባዔ በርካታ ልምዶች የተቀሰሙበት እንደነበር ተገልፅዋል።