ክፍት የከፍተኛ ስራ አመራር ቦታ ማስታወቂያ

 

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንት ሆኖ ለማገልገል ፍላጎቱና ብቃቱ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ የላቀ ውጤት ያመጣችውን/ውን ተወዳዳሪ በቦታው ለመመደብ ይፈልጋል፡፡ 

1. አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፤ 

1.1 የትምህርት ደረጃ፡ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ወይም ሁለተኛ ድግሪ (ዲግሪ) (MA/MSc) ያለዉና/ያላት ቢያንስ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማእረግ ያገለገለ/ያገለገለች የሚገኝ/የምትገኝ፤ 

1.2 የሥራ ልምድ፡በከፍተኛ ትምህርት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በከፍተኛ አመራር/ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ 

1.3 ስትራተጂያዊ እቅድ ማቅረብ፡አመልካቾች በአካደዳሚክ ዘርፉ ስለሚሰጡት አመራር ከ10 ገጽ ያልበለጠ ስትራተጂያዊ እቅድ በፅሁፍ ማቅረብ እና በሚዘጋጀው መድረክ ላይ ገለፃ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፤ (ስትራተጂያዊ እቅዱ ከቢሮው የሥራ ኃላፊነቶች እና ግዴታዎች የሚመነጩ መሆን ይኖርባቸዋል)   

1.4 ፆታ፡ወንዶችንና ሴቶችን  የሚያጠቃልል ሲሆን፣መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴቶች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፤ 

2. ተፈላጊ ክህሎቶች 

አመልካቾች የአመራር ክህሎት፣አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን የማመንጨትና የተግባቦት ክህሎት አሟልተው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፣

3. ተፈላጊ ስነምግባራዊ ባህሪያት

አመልካቾች ከስነ ምግባር ጉድለቶች የፀዱ፣በመልካም ባህርያቸው የተመሰከረላቸው መሆን አለባቸው፤

4. የምደባ ሁኔታ

የተመረጠው/ችው አመልካች አራት አመታት አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ/የምትመራ ሲሆን እንደ የአስፈላጊነቱና የአመራር ብቃትና ችሎታ ላይ ተመስርቶ ለተጨማሪ አራት አመታት ሊራዘም ይችላል፡፡

5. ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ስኬል መሰረት፤

6. የማመልከቻ ጊዜ

አመልካቾች ማመልከቻቸውን፣ ካሪኩለም ቪቴ (CV)  ኦሪጅናል የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር እንዲሁም የሚወዳደሩበትን የኃላፊነት ዘርፍ በሚመለከት  10 ገጽ ያልበለጠ ስትራተጂያዊ እቅድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ  መጋቢት 09 ቀን 2010 ዓ.ም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ  ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

7. የማመልከቻ  ማቅረቢያ ቦታና የማቅረቢያ መንገዶች

·         በግንባር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት (አንደኛ ፎቅ፣ቢሮ ቁጥር 102 ) እና አዲስ አበባ  ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ፊትለፊት 20 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮ በመቅረብ

·         በፖስታ ሳጥን ቁጥር 378 ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ወይንም ፖስታ ሳጥን ቁጥር 5241ጅማ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮ አዲስ አበባ በመላክ

8. ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎች ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል

·         በስልክ ቁጥር +251 47 111 1457

·         በሞባይል ስልክ ቁጥር +251 917821075 እና +251911 864378 / 0911998173/ 0111550621

·         በኢሜይል አድራሻ temesgenmereba@yahoo.com እና keteboab@yahoo.com

·         በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት www.ju.edu.et

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ ለመመልከት ይህን ይጫኑ