Developmental Team Training Program

ጅማ ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 7 2013ዓ.ም
***************************************************
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግሮች በመቅረፍ ጉዞዉን ቀጥሏል፡፡
በበቾ ቦሬ ቀበሌ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በእድገት ተኮር የልማት ቡድን (DTTP) ፕሮግራም የሁለተኛ ዲግሪ የጤና ተማሪዎች እና በአካባቢዉ ማህበረሰብ ትብብር የተገነባ የጤና ኬላ ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል፡፡
የጤና ኬላዉ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆንና የማህበረሰቡን የጤና ችግር ከመቅረፍ አኳያ ጉልህ አስተዋፅዖ ያበረክታል ተብሏል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በህረተሰብ አቀፍ ትምህርት ፍልስፍናዉ እየተመራ የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በመንከባከብና በአግባቡ በመጠቀም ራዕዩን ለማሳካት የበኩላቸዉን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ የአከባቢዉ ማህበረሰብ ገልጾል፡፡