ለሃገር ጥሪ ምላሽ የመስጠት አካል የሆነው ድጋፍ ዛሬም ተደርጉዋል። ዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ ዋጋቸው ከ 600 ሺህ ብር በላይ የሆነ 80 ኩንታል ምስር እና 80 ኩንታል የቅንጬ እህል ድጋፍ አድርጉዋል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ይህ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንደሆነ ገልፀው መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚወስደው እርምጃ ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር፣ የመማር ማስተማር እና የተቀናጀ ማህበረሰብ አገልግሎትን ተደራሽነት ማረጋገጥ የሚችሉት የሃገር ሠላም ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ እና ለዚህም ስኬት ዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደሚወጣ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ገልፀዋል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬ ዝደንት ዶር ቀነኒሳ ለሚ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለውና የዩኒቨርሲቲው ሠታራተኞች የገቢትን ድጋፍ የማድረግ ቃል በፍጥነት ተፈፃሚ እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል።
ከትላንት በስቲያ በተካሄደው የሠራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ውይይት ሠራተኞች በገንዘብ፣ በእውቀትና በሙያቸው ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውና ዩኒቨርሲቲውም 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።