የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለቀረበው ሃገራዊ ጥሪ ምላሽ የደም ልገሳ አድርገዋል።
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው እለት ከሠራተኞች ጋር ባደረገው ውይይት 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉና የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችም በበከåላtው በእውቀት፣ በገንዘብና በደም ልገሳ እንዲሁም ሙያዊ አገልግሎት ለማበርከት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
የዚሁ አበርክቶት አካል የሆነውን የደም ልገሳ ስነ-ስርዓት ባከናወኑበት ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እንደተናገሩት የደም ልገሳው በሃገራችን የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሂደት ላይ ለሚከሰቱ ጉዳቶች አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ፕሬዝደንቱ በንግግራቸው እንደ ዜጋ፣ እንደ ማህበረሰብ እና እንደ ተቋም ሊደረጉ የሚገባቸውን ድጋፎች እንደሚያደርጉ ገልፀው በችግር ግዜ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ግዜያትም ተመሳሳይ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፤ ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ እንደሆነና የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ እንዳቋቋመገልፀዋል።
ዶ/ር ጀማል እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ለሀገር ጥሪ ምላሽ የመስጠት የካበተ ልምድ ያለው መሆኑን አስታውሰው ሙያዊ ድጋፎች ባስፈለጉበት ቦታዎች ለመስጠት ዝግጁነት አለ ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እባላት ደም በመለገስ ለሃገራዊ ጥሪው የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ጥቃቱን በማውገዝ መንግስት አየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ እንደሚደግፉ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።