ጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ለሻሎም ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡
ብዛታቸዉ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ የሆኑ የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና አልባሳት በድጋፍ መልክ ተሰጥተዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር መሀመድ መጫ የተደረገዉ ድጋፍ ግዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘላቂ ባለመሆኑ ወደፊት በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተቀበለዉ ሻሎም ግብረሰናይ ድርጅትም በጅማ ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች ለሚገኙ አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያከፋፍል እንደሆነ ተገልፅዋል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማህበረሰቡ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የሚያደርገዉ ድጋፍ ዘላቂነት እንዲኖረዉ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን ወደፊትም መሰል ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡