የዉኀ ስነ-ምህዳር ጥበቃ እና እንክብካቤ

የዉኀ ስነ-ምህዳር ጥበቃ እና እንክብካቤ
ሰኔ 18/ 2013 ዓም፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ
****************************************
ግልገል ግቤ ቁጥር አንድን ታሳቢ ያደረገ የተፋሰስ ልማትና የዉኀ ስነ-ምህዳር ጥበቃ እና እንክብካቤ ፕሮጀክት ላይ ያተኮረ ወርክሾፕ ተካሄደ፡፡
በወርክሾፑ ላይ የዉይይት መነሻ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በጅማ ከተማ ያሉ ተፋሰሶች፣ ረግረጋማ ቦታዎች እና የዉሃ ስነ-ምህዳሮች ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የዉሃ፣ የአየር ንብረት ለዉጥን ሚዛን የመጠበቅ፣ ለመዝናኛ እና ለተለያዩ የግብርና ስራዎች ግልጋሎት ሲሰጡ የነበሩ መሆናቸዉ ተነስቷል፡፡
ሆኖም በከተማ እድገት፣ በኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና በህዝብ ብዛት መጨመር ምክንያት እንዚህ ስነ-ምህዳሮች የመበከል ችግር ስላጋጠማቸዉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እክል ፈጥሯል፡፡
ከተቋማት የሚወጣ፣ ከመፀዳጃ ቤቶች፣ ከመኪና አጥበት የሚወጡ ቆሻሻዎች እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ችግሮች በጥናታዊ ጥሁፉ የቀረቡ ዋና ዋና ችግሮች ናቸዉ፡፡ እነዚህም ችግሮች በአዌቱ፣ በቦዬ እንዲሁም ኪቶ እና ሌሎች ተፋሰሶች ላይ የሚስተዋሉ በመሆናቸዉ በግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
ግድቡን ከብክለት ለመጠበቅና የዉሃ ስነ-ምህዳርን ለማልማትና ለመንከባከብ የተቀናጀ ስራ በተፋሰስ ልማት ባለስልጣን የኢኮ-አግሮሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሐንስ ዘርይሁን ግልገል ጊቤ አንድ የሚደርስበትን የዉሃ ነክ ችግሮች ምንጫቸዉን በመለየት የተፈጥሮ ሂደትን ማዕከል ባደረገ ችግር ፈቺ ሳይንስ በካይ ነገሮችን ከምንጫቸዉ የማድረቅና ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ የመቀየር ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እና የተፋሰስ ልማት ባለስልጣን በጋራ የሚተገበር ሲሆን ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት በሙሉ የሚሳተፉበት እንደሆነም ታዉቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለተፋሰሶች፣ ለዉሃ አዘል መሬቶች፣ ለግብርና ስራዎች፣ ለአየር ንብረት ለዉጥ ስራዎችና ልማት የሚኖረዉ ፋይዳ የጎላ አድንደሆነ ተነግሯል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት አዳራሽ በተካሄደዉ ወርክሾፕ ላይ ከጅማ ዩኒቨርሰቲ፣ ከተፋሰስ ልማት ባለስልጣን ከጅማ ዞን እና ጅማ ከተማ የተዉጣጡ ባለሙያዎችና የሥራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡