በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ትግበራ ግምገማ ለሁለት ቀናት ሲያደርግ የቆየው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣው ገምጋሚ ቡድን፣ አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን ከምስጋና ጭምር ገልጾ ጥቂት ክፍተት በታየባቸው ቦታዎች ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት አስታዉቋል፡፡
የዩኒቨርሲተው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በበኩላቸው፣ የኮቪድ-19ን ስርጭት ከመከላከል አçያ እጅግ አበረታች ስራ መሰራቱን ገልጸው፣ መልካም ተሞክሮዎችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ለማረም የበለጠ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገምጋሚ ቡድን በትላንትናዉ ዕለት በዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ሀብታሙ እየተመራ፣ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል ትግበራው በምን ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተወያይቶም ነበር፡፡
በዚሁ መሰረት ወደ መስክ ቅኝት የገባው ገምጋሚ ቡድኑ፣ ከጉብኝቱ ያገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ፣ ዩኒቨርሲቲዉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሰራው ስራ መርካቱን ገልÊüል፡፡ በመስክ ቅኝት ወቅት የተስተዋሉ ክፍተቶች መስተካከል እንደሚገባቸውም ቡድኑ ጠቁNýል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በተለይም ፕሬዝደንቱ ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ጠንካራ ጎናችንን የበለጠ አጠናክረን፣ በአዳዲስ ትግበራዎች በመታገዝ፣ መሻሻል ያለባቸውን ነገሮች የበለጠ እያሻሻልን የዩኒቨርሲቲውንና የከተማውን ማህበረሰብ ህይወት ለመታደግ በላቀ ቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል፡፡ ከራስችን አልፈን በሀገር ደረጃ ተጽዕኖ ለመፍጠርም ጭምር እንተጋለን በማለት ሀሰባቸውን ደምድመዋል፡፡