ኮሚቴው ዛሬ በ09/07/2011 ዓ. ም. ባካሄደው ስብሰባው የአመልካቾችን የትምህርት ደረጃ የመለየት፣ የስራ ልምዳቸውን የመለየትና ለስራ ልምዳቸው ደረጃ የመስጠት ስራ አከናውኗል፡፡ ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ከተቀበላቸው 10 (አስር) ተወዳዳሪዎች መካከል 9 (ዘጠኝ) ተወዳዳሪዎች ብቻ በውድድሩ እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
- ፕሮፌሰር ቂጤሳ ሁንዴራ
- ፕሮፌሰር አርጋው አምበሉ
- ዶ/ር አብዱ አባጊቤ
- ዶ/ር ጀማል አባፊጣ
- ዶ/ር ዘይኑ አህመድ
- ዶ/ር እውነቱ ሀይሉ
- ዶ/ር ሱልጣን ሱሌማን
- ዶ/ር ናቃቸው ባሹ እና
- ዶ/ር ገመዳ አበበ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ናቸው፡፡
እንዲሁም ለአስተዳደርና የተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ የተቀበላቸው አራት አመልካቾች በውድድሩ እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡ እነዚህም፡-
- ዶ/ር ደሳለኝ በየነ
- ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ
- ዶ/ር ተክሉ ታፈሰ እና
- ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ ናቸው፡፡
ኮሚቴው