የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትንና የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንትን ለማስመረጥ የተቋቋመው የእጩ መልማይና ምርጫ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና አስተዳዳሪዎች አሰያየምን ለመደንገግ የወጣውን መመርያ መሠረት በማድረግ ለዪኒቨርሲቲው ፕሬዚደንትነት ያመለከቱ እጩ ተወዳዳሪዎችን የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ፣ ፓናል ኢንተርቪውና Vision Plan እንዲያቀርቡ በማድረግና መመርያውን ተከትሎ በማስገምገም የአመልካቾችን የመጨረሻ ውጤት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ እንደተመለከተው መሆኑን ይገልጻል፡፡
S. No. |
NAME OF THE CANDIDATES
|
TOTAL RESULT (100%) |
|
1. |
Dr. Jemal Abafita |
75.48 |
|
2. |
Dr. Sultan Suleyman |
73.34 |
|
3. |
Dr. Nakachew Bashu |
71.04 |
|
4. |
Professor Argaw Ambelu |
70.47 |
|
5. |
Dr. Abdu Abagibe |
70.3 |
|
6. |
Professor Kitessa Hundera |
69.05 |
|
7. |
Dr. Gemeda Abebe |
67.34 |
|
8. |
Dr. Ewinetu Hailu |
64.38 |
|
9. |
Dr. Zeinu Ahimed |
59.31 |
|
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና አስተዳዳሪዎች አሰያየም መመርያ አንቀጽ 6.4 (2 እና 3ሠ) መሠረት ከላይ በሰንጠረዡ ከተዘረዘሩትና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት የመጀመርያዎቹ አምስት እጩ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የሚላክ ሲሆን ቦርዱም በእጩ መልማይና ምርጫ ኮሚቴ አማካይነት ከመቶ ተሰልቶ የቀረበለትን የተወዳዳሪዎች ውጤት ወደ 80 በመቶ ቀይሮና የራሱን ግምገማ ከ20 በመቶ ጨምሮ በማስላት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የሚወጡትን እጩዎች የራሱን ምክረ-ሃሳብ በማካተት ለሚኒስቴሩ በማቅረብ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት እንደሚየሾም ይጠበቃል፡፡
በሌላ በኩል ኮሚቴው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንቱ የምርጫ ሂደት እንዳልተጠናቀቀ እየገለጸ ውጤቱን በሂደት የሚያሳውቅ መሆንን ማስገንዘብ ይወዳል፡፡
ኮሚቴው