የነገውን ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እንገንባ

የነገውን ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እንገንባ
ግንቦት 10/ 2013 ጅማ ዩኒቨርሲቲ
*****************************************
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የአሰር ዓመት ስትራቴጅክ (መሪ) እቅድ (Strategic Plan) (እአአ 2021-2030) ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ ተገባ፡፡ መሪ እቅዱ ወደ ስራ ክፍሎች ወርዶ ከአንድ ወር ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ጉዳዩ በሚመለከተው በእያንዳንዱ ሰራተኛ በዝርዝር ታቅዶ ይደራጅና ወደ ትግበራ ይገባል፡፡
የመሪ እቅዱን አንçር ጉዳዮች ለካውንስል አባላት ያቀረቡት የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶር ገመችስ ፍሌ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጅክ ማኔጅመንት ሲኒየር ዳርክተር አቶ ብርሃኑ መገርሳ ናቸው፡፡
በስተራቴጂክ እቅዱ ላይ ውይይት እንዲካሄድ የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር ጀማል አባፊጣ፣ ይህ እጅግ የተደከመበት ሰነድ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ጉዞ ከእርምጃ ወደ እመርታ ያሸጋግረዋል፣ በመሆኑም ሁላችም በባለቤትነትና ሃላፊነት በተሞለበት ሁኔታ ወደ ተግባር መቀየር ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በውይይቱ ሂደት፣ በካውንስሉ ዓባላት በስትራቴጅክ እቅድ ሰነዱ፣ ቢካተትና ትኩረት ቢሰጠው የተባሉ ሀሳቦች ተነስተው በቂ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በማጠቃለያውም ይህንን ጥልቅና የካበተ የስተራቴጅክ እቅድ ሰነድ ላዘጋጀው ቡድን፣ የዩኒቨርሲቲው ፐሬዝዳንት ምስጋና አቅርበው የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥተዋቸዋል፡፡