የአገሪቷ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮቪድ 19 ወርሺኝን ለመከላከል የሚያግዙ የሰሯቸውን የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ በዛሬው እለት በጅማ ዪኒቨርሲቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ ። ዝግጅቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ያስጀመሩት ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት; ሚኒስትር ድኤታዎች የዩኒቨርስቲ ፕሬዘደንቶችና አመራር አባላት ተሳትፈዋል ።የአውደ ርዕይ ዝግጅቱ እስከ ማክሰኞ መስከረም 12/2013 ዓ.ም ይቀጥላል ።
ጅማ ዩኒቨርሲቲ