ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለገበታ ለሀገር መርሃ-ግብር ዩኒቨርሲቲው 20 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው በሙያ፣ በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ፣ በማማከር እና በሌሎች በአይነት በሚገለፁ ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀው በገንዘብ ደግሞ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከሠራተኞችና የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ጋር በመወያየት ሌሎች ድጋፎችንም ያደርጋል ብለዋል።

ፕሬዘደንቱ ይህንን ያሉት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ለማስጀመር እየተደረገ ባለው የምክክር መድረክ ላይ የገበታ ለሀገር መርሃ-ግብር ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡

በጥቅሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለገበታ ለሀገር መርሃ-ግብር ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ያደርጋል።

ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም በዚሁ መነሻነት የየራሳቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቁዋል።