እንኳን ደህና መጣችሁ

እንኳን ደህና መጣችሁ!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 19/2013ዓ.ም
******************************************
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ በአካል ጉዳተኝነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡
ስልጠናዉ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራር አካላት እና በተማሪዎች ካዉንስል ስር ያሉ ክለቦችን ለሚመሩ ተማሪዎች ነዉ የሚሰጠዉ፡፡
ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ጥበቃና ደህንነት ሰራተኞችም ተመሳሳይ ስልጠና ባለፉት ሁለት ቀናት ሲሰጥ ነበር፡፡
የስልጠናዎቹ ዓላማ፣የሰልጣኞቹን በአካል ጉዳተኝነት ላይ ያላቸዉን ግንዛቤ በማጎልበት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የበለጠ እንዲረዱ በማስቻል ተማሪዎቹ እንደሌሎቹ ጉዳት አልባ ተማሪዎች ዉጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል እና ዩኒቨርሲቲዉን አካታች/inclusive የማድረግ ሂደትን ለመደገፍ ነዉ፡፡
በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠዉ ትምህርት ዳግም ሲጀመር በድጋሚ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ የመጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል ሃላፊ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ የECDD ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጃፋር ሎላ እንዳሉት የፕሮግራሙ ዓላማ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ በዩኒቨርሲቲዉ ያሉ አገልግሎቶች የት የት እንዳሉ እና ችግር ሲያጋጥማቸዉ ማንን ማነጋገር እንዳለባቸዉ እንዲሁም እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ለማድረግ ነዉ፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎች አገልግሎት የሚያገኙበት ማዕከል ከፍቶ ወደ ስራ ከገባ ሰንበትበት ብሏል፡፡
አካል ጉዳተኛ ተማሪዎቹ በትምህርት ቆይታቸዉ ዉጤታማ እንዲሆኑና ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር የሚያግዙ የሳይኮ-ሶሻል እና ኮቪድ-19 ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መልዕክቶች ቀርበዋል፡፡
(ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት) በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ዲላ እና ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነዉ፡፡
የECDD ተወካይ አቶ ዮሐንስ ተክላይ ላለፉት ሁለት አመታት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በቁሳቁስ እና ስልጠና በመስጠት ድጋፍ ሲያደርግ እንደቀየ ገልፀዉ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ድጋፍ በትምህርት ላይ ያሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከተመረቁም በኋላ የተሻለ ደረጃ እስኪደርሱ ቀጣይነት አለዉ ተብሏል፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአካል ጉዳተኞች መገልገያ የሚሆን ልዩ ስፍራን በማዘጋጀቱ እንዲሁም ከበር ጀምሮ ለተማሪዎቹ ቅበላ የተደረገዉ ዝግጅትና አገልግሎት ምስጋና ተችሮታል፡፡