አሸንፈናል!

አሸንፈናል!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀምሌ 8/2013 ዓም
*****************************
በሀገራችን የመጀመሪያ በሆነው የሳይንስ ፈጠራ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ካሉ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በላቀ አፈፃፀም አንደኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሀገራችን ካሉ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች የላቀ አመራር በመስጠታቸውና ከፍተኛ ብቃት በማስመዝገባቸው የዩኒቨርሲያችን ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ አንደኛ በመውጣት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡
የሀዋሳ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ ሽልማት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ሶስት የፈጠራ ባለቤቶች ተሸላሚ ሆነዋል።
በላቀ የፈጠራ ውጤት አንደኛ በመውጣት የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 250 ሺህ ብር ተሸላሚ የጅማ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጀርሚያ ባይሳ እና ቦዔዝ ብርሃኑ ሲሆኑ ዶ/ር አዲሱ በፍቃዱ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 200 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።
በዚሁ ውድድር የጅማ ዩኒቨርሲቲዎቹ ደራርቱ ደረጀ እና ሽመልስ ንጉሴ እኩል ነጥብ በማምጣት የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 150 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።
በምርጥ መምህራን ሽልማት ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ሠርተፊኬት፣ ሜዳሊያ እና 25 ሺህ ብር ተሸላሚ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን ዶ/ር ሙሉእመቤት አበራ እና ዶ/ር ዮሐንስ ከበደ ሲሆኑ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና የ7 ሺህ ብር ተሸላሚዎች ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ተማሪዎች ሳባ ደስታ እና መስቀሉ ዳንኤል ሆነዋል።