በማህበረሰብ ዉስጥ ነን!

በማህበረሰብ ዉስጥ ነን!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ መጋቢት 17/2013ዓ.ም
*****************************************
በአዌቱ መንደራ፣ በጊንጆ ጉዱሩ እና በበቾ ቦሬ ቀበሌ ለማህበረሰቡ አግልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ፐሮጄክቶች በጅማ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ተገንብተው ለህብረተሰቡ ተላለፉ፡፡
ዩኒቨርሲቲያችን በህብረተሰብ አቀፍ ትምህርት የካበተ የብዙ አመታት ልምድና ክህሎት ባለቤት ነዉ፡፡
በመሆኑም፣ ዕድገት ተኮር የቡድን ስልጠና (DTTP) መርሃ ግብር በድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የሚተገበር የህብረተሰብ አቀፍ ትምህርትን ከግብ ማድረሻ መንገዶች አንደኛዉ ነዉ፡፡
በተለይም፣ DTTP እና ሌሎች ተግባራት የማህበረሰባችንን ችግር መለየት ብቻ ሳይሆን ችግሩን መመርመር እና የመፍትሄ አካል መሆንን ዋነኛ ግባቸው ነው፡፡፡፡
በዕደገት ተኮር የቡድን ስልጠና እዉን የሆኑ ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን ችግር ከመፍታት እና ማቃለል አንፃር ሚናቸዉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡
ባሳለፍነዉ ሳምንት ለማህበረሰቡ ከተላለፉ ፕሮጀክቶች መካከል በአዌቱ መንደራ ቀበሌ ለአካል ጉዳተኞች የሻወር (ገላ መታጠቢያ) እና መፀዳጃ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ከመኖሪያ አካባቢያቸዉ ተፈናቅለዉ በአሁኑ ግዜ በጊንጆ ጉዱሩ ቀበሌ ለሚገኙ ዜጎች የምግብ ማብሰያ ቤት እና በበቾ ቦሬ ቀበሌ ተገንብቶ ለህብረተሰቡ የተላለፈ የጤና ኬላ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡
እንዚህ ፕሮጀክቶች የማህበረሰባችንን የጤና ችግሮች ከመቅረፍና የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ፣ እንዲሁም በምግብ ማብሰል ሂደት የሚፈስሰውን ጉልበት ከመቀነስና ለአካል ጉዳተኞችና ዜጎች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያደርገዉን ጥረት በምርምር፣ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ በማገዝ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡