ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

logo for news

የጅማ ዩነቨርሲቲ መደበኛ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ሁሉም ድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባችሁ ጥቅምት 12 እና 13/2011ዓ.ም የሚፈጸም መሆኑን እየገለጽን በየኮሌጃችሁ እና ኢንስቲትዩቶቻችሁ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤቶች በግንባር በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድትፈጽሙ እናስታውቃለን፡፡

በተጨማሪም የመሰናዶ ትምህርታችሁን አጠናቅቃችሁ በ2011ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባችሁ የሚፈጸመው ጥቅምት 19 እና 20/2011ዓ.ም ስለሆነ በየተመደባችሁበት ካምፓስ በግንባር በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት