ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ቅደመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

logo for news_2

ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተከሰተዉ ችግር ጋር ተያይዞ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት በዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመማር ማስተማር ሂደት ለተወሰኑ ቀናት መቋረጡ ይታወሳል፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን አመራር፣ አካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች በተለያዩ ደረጃዎች ከተለያዩ አካላት ጋር ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታ እንዲፈጠር ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ የዩኒቨርሲቲያችን ሴኔት ዛሬ በ11/03/2012 ባደረገዉ ሁለተኛዉ አስቸኳይ ስብሰባ አሁናዊ ሁኔታዉን በመገምገም ትምህርት ለማስጀመር አስቻይ ሁኔታዎች በመፈጠራቸዉ ሰኞ 15/03/2012 ዓ.ም. ትምህርት እንዲጀመር ወስኗል፡፡

በመሆኑም፣ ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ከዓርብ ህዳር 12 እስከ 14/ 2012 ዓ.ም. በየካምፓሶቻችሁ ዳግም-ምዝገባ (Re-registration) በማካሄድ ሰኞ 15/03/2012 ዓ.ም. ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡፡

ጅማ ዩኒቨርሲቲ