Disability Support

Disability Support

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በርከት ያሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ እንደሆነ የታወቃል፡፡ እነዚህን የተለያዬ ጉዳት ያላቸዉን ተማሪዎች በአካታችነት ለማስተማር እና አገልግሎት ለመስጠት ዩኒቨርሲቲዉ የተለያዩ ድርጊቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል ህንፃዎችንና አከባቢዎችን ማመቻቸት፣ ለተማሪዎቹ ተስማሚ አጋዥ የትምህርት ቁሳቁስ ማቅረብ፣ እና የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት ይጠቀሳሉ፡፡እነኚህ ስራዎች በተቀናጀ ሁኔታ እንዲሰሩ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል በማቋቋም ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ባለፈዉ ቅዳሜ እና እሁድ (12-13/06/2013) አካል ጉዳተኞችን የማካተት እና የግንዛቤ ስልጠና በሚል ርዕስ በሁለት አደራሾች ለ30 የጥበቃና የደህንነት አባላት እንዲሁም በሌላ አዳራሽ ለ28 አካል ጉዳት አልባ ተማሪዎች ኢሲዲዲ (ECDD) ከሚባል ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡

አሁንም ሐሙስ እና ዓርብ (17-18/06/2013) በተመሳሳይ ርዕስ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራር አባላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የአሁኑ ስልጠና ያለመዉ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ የሚገኙትን የአስተዳደር እና የአካዳሚክ አባላት በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ (ፊላጎታቸዉ፣ ችሎታቸዉ፣ መብታቸዉ፣ ወዘተ ) ያላቸዉን ግንዛቤ ከፍ ማድረግ ይሆናል፡፡ ይህም የዩኒቨርሲቲዉን የአገልግሎት አሰጣጥ ለአካል ጉዳተኞች ይበልጥ ተደራሽ እና ምቹ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጃፈር ሎላ (ረ/ ፕሮፌሰር)

የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል አስተባባሪ