Disability Support Events

Disability Inclusion and Awareness Training launched by ECDD at Jimma University.
አካል ጉዳተኞችን ማካተት እና የግንዛቤ ስልጠና በጅማ ዩኒቨርሲቲ እንደቀጠለ ነዉ

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በርከት ያሉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ እንደሆነ የታወቃል፡፡ እነዚህን የተለያዬ ጉዳት ያላቸዉን ተማሪዎች በአካታችነት ለማስተማር እና አገልግሎት ለመስጠት ዩኒቨርሲቲዉ የተለያዩ ድርጊቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል ህንፃዎችንና አከባቢዎችን ማመቻቸት፣ ለተማሪዎቹ ተስማሚ አጋዥ የትምህርት ቁሳቁስ ማቅረብ፣ እና የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠት ይጠቀሳሉ፡፡እነኚህ ስራዎች በተቀናጀ ሁኔታ እንዲሰሩ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል በማቋቋም ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ባለፈዉ ቅዳሜ እና እሁድ (12-13/06/2013) አካል ጉዳተኞችን የማካተት እና የግንዛቤ ስልጠና በሚል ርዕስ በሁለት አደራሾች ለ30 የጥበቃና የደህንነት አባላት እንዲሁም በሌላ አዳራሽ ለ28 አካል ጉዳት አልባ ተማሪዎች ኢሲዲዲ (ECDD) ከሚባል ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡

አሁንም ሐሙስ እና ዓርብ (17-18/06/2013) በተመሳሳይ ርዕስ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራር አባላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የአሁኑ ስልጠና ያለመዉ በተለያዩ ኃላፊነት ላይ የሚገኙትን የአስተዳደር እና የአካዳሚክ አባላት በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ (ፊላጎታቸዉ፣ ችሎታቸዉ፣ መብታቸዉ፣ ወዘተ ) ያላቸዉን ግንዛቤ ከፍ ማድረግ ይሆናል፡፡ ይህም የዩኒቨርሲቲዉን የአገልግሎት አሰጣጥ ለአካል ጉዳተኞች ይበልጥ ተደራሽ እና ምቹ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጃፈር ሎላ (ረ/ ፕሮፌሰር)

የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል አስተባባሪ

 

March 26, 2021 GC
ECDD in collaboration with Jimma University launches two-days training for students with disabilities. The trainings are
1. Leadership Training
2. Rights of persons with Disabilities
Leadership Training is intended to equip the students with basic skills of leadership so that it would contribute to the effort to bring persons with disabilities to leadership position.
Training on Rights of persons with Disabilities on the other hand would increase their understanding about international and national legal documents about persons with disabilities. This will help them to exercise their rights.

Disability Inclusion and Awareness Training launched by ECDD at Jimma University. The current training was prepared for university Security staff and students without disabilities. It is intended that this training will enhance the participants knowledge about disability and thus pu them at a better position to support students with disabilities at the university.