ተማሪዎችን የመቀበል ሂደት አካል የሆነው የግቢ ጽዳትና ውበት ንቅናቄ ተካሂዷል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው አመት ሁለንተናዊ የግቢ ጽዳትና ውበት ለውጥ ለማምጣት አቅጣጫ አስቀምጦ የንቅናቄ መርሃ-ግብር አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ታውቋል። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጽዳትና ውበት ስራን በዛሬው እለት ሲያከናውን ውሏል። የተማሪዎች መኝታ፣ መመገቢያ፣ መማሪያ እና መዝናኛ […]
ዛሬም በጅማ ከተማ የተባበሩት አካባቢ በቀድሞ አጠራሩ ኢዲዲሲ ዉስጥ ለሚኖሩ ከ 450 በላይ አባወራዎች ፍራሾች፣ ምግብና ምግብ ነክ እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሁኔታ እና አጋጣሚዎች ለህብረተሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በዛሬዉ እለትም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክስ እና አስተዳደር ሰራተኞች ድጋፍ ግምታቸዉ ከ 500 ሺህ ብር በላይ የሆኑ ፍራሽ፣ የምግብ እህልና […]
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት ስር የሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ፡፡ ዉይይቱ የ2013ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላን አስመልክቶ ሊደረጉ ስለሚገባቸዉ ጥንቃቄዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ታዉቋል፡፡ የጥበቃና ደህንነት፣ የጠቅላላ አገልግሎት፣ የተማሪዎች መኝታ ተቆጣጣሪዎች፣ የተማሪዎች ካፍቴሪያ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ የስራ ክፍሎች፤ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሲመጡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከግምት ዉስጥ ያስገባ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን […]
የሃገር ሁለንተናዊ እድገትን ለማፋጠን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀምና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተነገረ፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በትብብር መስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ተፈራርመዋል፡፡ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የዩኒቨርሲቲዉን አብይ የትኩረት አቅጣጫ የሆኑት መማር […]
የኮቪድ – 19 ምላሽ የፈጠራ ስራዎች ዓውደ-ርዕይ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጉባኤ አስተባባሪዎች የእውቅና እና ምስጋና ፕሮግራም በሃጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ ማዕከል ተካሂዷል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በየደረጃው የሚገኙ ሰራተኞቹ ጥረትና ያልተቆጠበ አስተዋፅዎ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ አንድ ተቋም ያለሰራተኞቹ ትጋትና […]
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የካንሠር ህክምና መስጫ ማዕከል፤ አዮ የተቀናጀ አምቡላንስ አገልግሎት፤ የኦክስጅን ማምረቻ፣ ማጣሪያና ማስተላለፊያ ፕላንት፤ የጅዩ-ሲምቦና ህክምና ቁሳቁስ ዲዛይን ላብራቶሪ እና በባዮሜዲካል ማዕከል የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች በጉብኝቱ ምልከታ ከተካሄደባቸው መካከል ናቸው። ሚኒስትር ድኤታው በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው አዮ የአንድ […]
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የጅማ ከተማ ከንቲባና የዩኒቨርሲቲዉ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቲጃኒ ናስር እና የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የእለቱ ተመራቂዎችንና ቤተሰቦቻቸዉን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዉ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሀገራችን ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ መሆኑንና በተለይም በጤናዉ ዘርፍ […]
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ከፍተኛ ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመው የምልከታ ኮሚቴ ገለጸ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 11 ኮሚቴዎችን በማቋቋም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለመቀበል ምን ዝግጅት አድርገዋል በሚል ወቅታዊ አቋምን በመፈተሸ ላይ ይገኛል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት ተቋማቱ ከገፅ ለገፅ ትምህርት […]
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በጅማ ከተማ ለሚገኘው ሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሰበሰበው ሃያ ዘጠኝ ሺ (29፣000) ብር የሚያወጡ የምግብ (5 ኩንታል ጤፍ፤ የጣሳ ዱቄት ወተቶችን) እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለአረጋዊያም መርጃ ማዕከሉ አስረክቧል፡፡ በስነስርዓቱም ላይ የየኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የተገኙ ሲሆን፤ […]
(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 16፣2013 ዓ.ም) የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤን በማሻሻል የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ማዘመን የሚያስችል ፕሮግራም ይፋ ሆነ። የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል። አዮ አምቡላንስ (እናት አምቡላንስ) አገልግሎትም ስራውን በይፋ ጀምሯል። የአምቡላንስ አገልግሎቱ በጅማ ከተማ እና ዞን የሚገኙ ሁሉም አምቡላንሶች በአንድ ማዕከል ስር ሆነው አገልግሎት የሚሰጡበትን አሰራር […]