Author: erouser

ለሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በጅማ ከተማ ለሚገኘው ሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሰበሰበው ሃያ ዘጠኝ ሺ (29፣000) ብር የሚያወጡ የምግብ (5 ኩንታል ጤፍ፤ የጣሳ ዱቄት ወተቶችን) እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለአረጋዊያም መርጃ ማዕከሉ አስረክቧል፡፡ በስነስርዓቱም ላይ የየኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የተገኙ ሲሆን፤ […]

የአዮ የተቀናጀ የአምቡላንስ አገልግሎት ለድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ።

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 16፣2013 ዓ.ም) የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤን በማሻሻል የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ማዘመን የሚያስችል ፕሮግራም ይፋ ሆነ። የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል። አዮ አምቡላንስ (እናት አምቡላንስ) አገልግሎትም ስራውን በይፋ ጀምሯል። የአምቡላንስ አገልግሎቱ በጅማ ከተማ እና ዞን የሚገኙ ሁሉም አምቡላንሶች በአንድ ማዕከል ስር ሆነው አገልግሎት የሚሰጡበትን አሰራር […]

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና ቀረበላቸው

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 13፣ 2013ዓ.ም) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋና አቀረቡ። ፕሬዝደንቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ለሶስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠልና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ የተሠሩ የፈጠራ ስራዎች ዓውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ለዚህ ፕሮግራም ስኬታማነት የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ሃላፊነቶችን በመውሰድ ሲሰሩ ቆይተዋል። ዶ/ር ጀማል ስኬቱን ከአድካሚውና አስቸጋሪው […]

ለሶስት ቀናት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተካሔደው ዓዉደ-ርዕይ እና የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠልና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዓልሞ ሲመክር የነበረው መድረክ ተጠናቋል፡፡ የምክክር መድረኩ ገንቢ የሆኑ ግብዓቶች የተሰበሰቡበት፣ የከፍተኛ ትምህርትን ለማስቀጠል መሰረት የተጣለበትና በባለድርሻ አካላት የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነበር፡፡ ከዚሁ የውይይት መድረክ ጎን ለጎን በተካሔደውና 45 ዩኒቨርሲቲዎችና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በተሳተፉበት ዓዉደ-ርዕይ ላይ በቀረቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በቂ ልምድ የተወሰደባቸዉና በሀገር […]

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አረንጓዴ አሻራ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የወንድማማችነት፣ የፍቅር እና የሠላም አደባባይ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች አረንጉዋዴ አሻራቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ችግኝ በመትከል አሳርፈዋል። የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ […]

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለገበታ ለሀገር መርሃ-ግብር ዩኒቨርሲቲው 20 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው በሙያ፣ በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ፣ በማማከር እና በሌሎች በአይነት በሚገለፁ ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀው በገንዘብ ደግሞ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከሠራተኞችና የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ጋር በመወያየት ሌሎች ድጋፎችንም ያደርጋል ብለዋል። ፕሬዘደንቱ ይህንን ያሉት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ለማስጀመር […]

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከዚህ በፊት ከነበረው አሠራር ለየት ያሉ ተግባራት እንደሚከወኑ ተገለፀ።

(መስከረም 12፣ 2013 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ቅድመ ዝግጅትና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ላይ ትኩረቱን አድርጎ ዛሬም ቀጥሏል። የሪፎርሙ አካል የሆነው የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ተግባርን ከግብ ለማድረስ ከየትምህርት ተቋማቱ ጠንካራ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች ተመርጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ማዕከልነት የትምህርት ስርዓት መረጃን በማደራጀት የመረጃ ልውውጥን ለማዘመን ይሰራል ተብሏል። የሳይንስና ከፍተኛ […]

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኮቪድ-19 ምላሽ ፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

የአገሪቷ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮቪድ 19 ወርሺኝን ለመከላከል የሚያግዙ የሰሯቸውን የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ በዛሬው እለት በጅማ ዪኒቨርሲቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ ። ዝግጅቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ያስጀመሩት ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት; ሚኒስትር ድኤታዎች የዩኒቨርስቲ ፕሬዘደንቶችና አመራር አባላት ተሳትፈዋል ።የአውደ ርዕይ ዝግጅቱ እስከ ማክሰኞ […]

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኮቪድ-19 ምላሽ ፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

መስከረም 10፣ 2013 ዓም: የአገሪቷ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮቪድ 19 ወርሺኝን ለመከላከል የሚያግዙ የሰሯቸውን የፈጠራ ስራዎች አውደ-ርዕይ በዛሬው እለት በጅማ ዪኒቨርሲቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ ። ዝግጅቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ ያስጀመሩት ሲሆን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት; ሚኒስትር ድኤታዎች የዩኒቨርስቲ ፕሬዘደንቶችና አመራር አባላት ተሳትፈዋል ።የአውደ […]