የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የካንሠር ህክምና መስጫ ማዕከል፤ አዮ የተቀናጀ አምቡላንስ አገልግሎት፤ የኦክስጅን ማምረቻ፣ ማጣሪያና ማስተላለፊያ ፕላንት፤ የጅዩ-ሲምቦና ህክምና ቁሳቁስ ዲዛይን ላብራቶሪ እና በባዮሜዲካል ማዕከል የሚገኙ የፈጠራ ስራዎች በጉብኝቱ ምልከታ ከተካሄደባቸው መካከል ናቸው። ሚኒስትር ድኤታው በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረው አዮ የአንድ […]
የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የጅማ ከተማ ከንቲባና የዩኒቨርሲቲዉ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቲጃኒ ናስር እና የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የእለቱ ተመራቂዎችንና ቤተሰቦቻቸዉን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዉ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሀገራችን ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ መሆኑንና በተለይም በጤናዉ ዘርፍ […]
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያደርገውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን ከፍተኛ ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተቋቋመው የምልከታ ኮሚቴ ገለጸ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 11 ኮሚቴዎችን በማቋቋም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ለመቀበል ምን ዝግጅት አድርገዋል በሚል ወቅታዊ አቋምን በመፈተሸ ላይ ይገኛል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት ተቋማቱ ከገፅ ለገፅ ትምህርት […]
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በጅማ ከተማ ለሚገኘው ሰው ለሰው የህጻናትና አረጋዊያን መርጃ ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት ከመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች በሰበሰበው ሃያ ዘጠኝ ሺ (29፣000) ብር የሚያወጡ የምግብ (5 ኩንታል ጤፍ፤ የጣሳ ዱቄት ወተቶችን) እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለአረጋዊያም መርጃ ማዕከሉ አስረክቧል፡፡ በስነስርዓቱም ላይ የየኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የተገኙ ሲሆን፤ […]
(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 16፣2013 ዓ.ም) የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤን በማሻሻል የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ማዘመን የሚያስችል ፕሮግራም ይፋ ሆነ። የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ዝግጅት በጅማ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል። አዮ አምቡላንስ (እናት አምቡላንስ) አገልግሎትም ስራውን በይፋ ጀምሯል። የአምቡላንስ አገልግሎቱ በጅማ ከተማ እና ዞን የሚገኙ ሁሉም አምቡላንሶች በአንድ ማዕከል ስር ሆነው አገልግሎት የሚሰጡበትን አሰራር […]
(ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 13፣ 2013ዓ.ም) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋና አቀረቡ። ፕሬዝደንቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ለሶስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ሲካሄድ በቆየው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማስቀጠልና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ የተሠሩ የፈጠራ ስራዎች ዓውደ ርዕይ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ለዚህ ፕሮግራም ስኬታማነት የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ሃላፊነቶችን በመውሰድ ሲሰሩ ቆይተዋል። ዶ/ር ጀማል ስኬቱን ከአድካሚውና አስቸጋሪው […]
የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠልና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ዓልሞ ሲመክር የነበረው መድረክ ተጠናቋል፡፡ የምክክር መድረኩ ገንቢ የሆኑ ግብዓቶች የተሰበሰቡበት፣ የከፍተኛ ትምህርትን ለማስቀጠል መሰረት የተጣለበትና በባለድርሻ አካላት የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነበር፡፡ ከዚሁ የውይይት መድረክ ጎን ለጎን በተካሔደውና 45 ዩኒቨርሲቲዎችና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በተሳተፉበት ዓዉደ-ርዕይ ላይ በቀረቡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች በቂ ልምድ የተወሰደባቸዉና በሀገር […]
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርካቶ፣ ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች አረንጉዋዴ አሻራቸውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ችግኝ በመትከል አሳርፈዋል። የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት እና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ […]
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ለገበታ ለሀገር መርሃ-ግብር ዩኒቨርሲቲው 20 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው በሙያ፣ በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ፣ በማማከር እና በሌሎች በአይነት በሚገለፁ ተግባራት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀው በገንዘብ ደግሞ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከሠራተኞችና የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ጋር በመወያየት ሌሎች ድጋፎችንም ያደርጋል ብለዋል። ፕሬዘደንቱ ይህንን ያሉት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ለማስጀመር […]
(መስከረም 12፣ 2013 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ቅድመ ዝግጅትና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ላይ ትኩረቱን አድርጎ ዛሬም ቀጥሏል። የሪፎርሙ አካል የሆነው የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ተግባርን ከግብ ለማድረስ ከየትምህርት ተቋማቱ ጠንካራ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች ተመርጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ማዕከልነት የትምህርት ስርዓት መረጃን በማደራጀት የመረጃ ልውውጥን ለማዘመን ይሰራል ተብሏል። የሳይንስና ከፍተኛ […]